የ“ኤልኒኖ” ክስተት
በመኮንን ተሾመ ቶሌራ
የኤልኒኖ ስጋት እያንዣበበ በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ከአባላት እና ከአጋሮች ድርጅቶቹ ጋር በመሆን ካሁኑ ትንበያዎችን መሰረት ያደረገ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል
የአየር ሁኔታዉ መገለባበጥ በደቡብ አፍሪካ ፣ በመካከለኛው አሜሪካ እና በሩቅ ምስራቅ እስያ ሊኖር የሚችለዉን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ ያሳያል
ኤልኒኖ እና ላኒና በፓስፊክ ውቅያኖስ ውስጥ በሚከሰት ከፍተኛ ሙቀትና ቅዝቃዜ ምክንያት የሚከሰቱ የአየር ንብረት መለዋወጦች ሲሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ሁኔታ ላይ የራሳቸዉን ከፍተኛ ተፅእኖ የሚያደርሱ ናቸዉ።
ላኒና በደቡብ አሜሪካ ሞቃታማ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ ላይ የውቅያኖስን ውሃ በጣም በማቀዝቀዝ የሚገልጽ የአየር ንብረት ሁኔታ ነው። የኤልኒኖ ክስተት በአንፃሩ ከፔሩ የባሕር ዳርቻ ወጣ ያለ ማዕከላዊ እና ምስራቅ የፓስፊክ ውቅያኖስ ውሀዎች የሙቀት መጠን ልዩ ጭማሪ ነው ፡፡ የሃይድሮፊስ እና የከባቢ አየር ከፍተኛ ሚዛን መዛባት የሚያስከትለው የአየር ንብረት ክስተት ውጤት ነው።
ይህ የአየር ሁኔታ ከ 8 እስከ 13 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በማደግ ከ 1 እስከ 6 ዓመት በሚለዋወጥ መደበኛ ያልሆነ ድግግሞሽ ይከሰታል ፡፡ ስሙ በፔሩ ዓሣ አጥማጆች የተሰጠው ሕፃኑን ኢየሱስን በመጥቀስ ነበር ፣ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ በገና አካባቢ ወደ ከፍተኛ ጥንካሬ ይደርሳል ፡፡
ላኒና ከረጅም ጊዜ የሶስት አመት ቆይታ በኋላ ዘንድሮ ከአለም አቀፉ የከባቢ አየር ሁኔታ ትእይንት ወጥቷል፣ ወደ ኤልኒኖ ለመሸጋገር እድሉንም ፈጥሯል፣ ይህም የአየር ሁኔታ በተቃራኒው የሚያሰራጭ ነው። ያ ለአንዳንድ በድርቅ ለተጎዱ እንደ አፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች እፎይታ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በሌሎች የአፍሪካ ክፍሎች፣ መካከለኛው አሜሪካ እና ሩቅ ምስራቅ እስያ ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል
ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ችግር የተጋለጡ ሰዎችን ቁጥር ግምት ውስጥ በማስገባት የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት (ኤፍ.ኦ.ኦ) በተለይ ለኤልኒኖ ተጋላጭ የሆኑትን አካባቢዎች እና አደጋውን ለመቅረፍ ግምታዊ ዕርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል አሳውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ FAO የአለም አቀፍ መረጃ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች የገበያ እና የንግድ ክፍል እና የአየር ንብረት ለውጥ ክፍል ደቡብ አፍሪካ ፣መካከለኛው አሜሪካ እና ካሪቢያን እና አንዳንድ የእስያ ክፍሎች አሳሳቢ መሆናቸውን አዲስ ዘገባው አመልክቷል ። በእነዚህ የአለማችን ክልሎች ውስጥ ያሉ ሀገራት ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ችግር ያጋጥማቸዋል እና ዋና ዋና የሰብል ወቅቶች በተለመደው የኤልኒኖ የአየር ሁኔታ እና ደረቅ ሁኔታዎች ምርታቸው ይስተጓጎላል። የደቡብ አሜሪካ ሰሜናዊ አካባቢዎችም የመድረቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፣ አውስትራሊያ ሀይለኛ የዝናብ ሁኔታ ያጋጥማታል ተብሎ ተሰግቷል።
“የቅድሚያ ማስጠንቀቂያዎችን በማየት ማለት ቀደም ብሎ እና ግምታዊ እርምጃ መውሰድ አለብን ማለት ነው፣ እናም አባሎቻችንን በእነዚህ ጥረቶች፣ አቅም በሚፈቅደው መጠን እንደግፋለን።” ብሏል FAO.
እ.ኤ.አ. በ2015 እና 2016 በተከሰተው የኤልኒኖ ክስተት በ23 ሀገራት ውስጥ ከ60 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ FAO ከአባላት ሀገራት ጋር በትጋት የሚችለውን አድርጎ ነበር። እንደ የማህበረሰብ ዘር መደብሮችን ማቋቋም፣ ስልታዊ የምግብ ክምችት መገምገም እና የእንስሳት ጤና ክትትል ዘመቻዎችን ማጠናከር ያሉ ወቅታዊ ስራዎችን ለማፋጠን መደበኛ የአሰራር ሂደቶች ተቀርፀዋል ሲልም አክሎ ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) በቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ደቡብ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ዚምባቡዌ፣ ፊሊፒንስ፣ ፓኪስታን እና መካከለኛው አሜሪካ የድርቅ አደጋን ለመከላከል Anticipatory Action ፕሮቶኮሎችን አዘጋጅቷል እናም ከመንግስታት እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ቀደም ብሎ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን አጠንቋል ።
የኤልኒኖ ክስተት ተፅእኖና ክብደቱ የት ሊሆን እንደሚችል በትክክት ያለማወቅ ችግር
ከሰኔ ጀምሮ የኤልኒኖ ክስተት የመከሰት እድልን ከፍ ካደረጉት የቅርብ ጊዜ ትንበያዎች አንፃር፣ FAO የተጎዱትን ሀገራት ለመደገፍ የመነሻ ዝግጅቶችን በማካሄድ ላይ ነው።
የ FAO አግሮሜትሮሎጂስት ኦስካር ሮጃስ “በዚህ ነጥብ ላይ ያሉ ትንበያዎች ግልጽ ናቸው ነገር ግን በግንቦት – ሰኔ – ሐምሌ ላይ በሚኖረው ዝቅተኛ ኃይል ምክንያት የሚኖረውን ሁኔታ ለማወቅ ትንሽ ያስቸግራል።” ብለዋል።
የኤልኒኖ ክስተቶች በአብዛኛው ከሁለት እስከ ሰባት አመታት የቆይታ ጊዜ ይኖራቸዋል። የላኒና እና ሌሎች ክስተቶች ደግሞ በመካከል ባለው ዓመታት ብዙ ጊዜ ይከሰታሉ። በፓስፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ምክንያት የተተነተነው ኤልኒኖ በብዙ የአለም ክፍሎች በሙቀት እና በዝናብ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ ድርቅን፣ ጎርፍ እና አውሎ ነፋሶችን ጨምሮ ከባድ የአየር ክስተቶችን ያስከትላል።
የኤልኒኖ ክስተቶች እና ተፅዕኖዎች ፈጽሞ ተመሳሳይ ባይሆኑም፣ ተመሳሳይ ጉዳት ያደርሳሉ። የ FAO እየሰራ ያለው ስለሁኔታው በእጽዋት ሁኔታዎች ላይ ለውጦችን በአለም አቀፍ የሰብል መሬቶች ካርታ ማዘጋጀት እና ይህንን ትንታኔ ከሰብል የቀን መቁጠሪያዎች ጋር በማጣመር የዝናብ እጥረት በምርት ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በተሻለ ለመረዳት ነወ። እንደ FAO ከሆነ ኤልኒኖ በውሀ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ በሰብል የህይወት ዑደት ውስጥ ከሚያደርሰው ይለያያል። ይህ አካሄድ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን ቦታዎች – ደረቅ ሁኔታዎች በጠቅላላው የሰብል ዑደት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩትን – እና መተግበር ያለባቸውን የስራ አይነት ለመለየት ይረዳል።
አደጋዎቹን በቅርበት ሞኒተር ማድረግ
የዝናቡ ሁኔታ በአርጀንቲና እና በምስራቅ እስያ አቅራቢያ ላሉ ገበሬዎች ጥሩ እፎይታ ቢሆንም፣ ኤልኒኖ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊያስከትል ስለሚችል ግብርናን ሊጎዳ እና የበሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምር ይችላል። ለአራት ዓመታት ያህል ከባድ የዝናብ እጥረት ካጋጠማው እና ምንም እንኳን ዝናብ ቢመለስም በማንኛውም ጊዜ መልሶ ማገገም ረጅም ጊዜ የሚወስድበት ምስራቅ አፍሪካ ጋር በተያያዘ FAO የመረመረው ልዩ ሁኔታ ነው።
አውስትራሊያ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ፣ ሁሉም ዋና ዋና የእህል አምራቾች እና ላኪዎች ሲሆኑ ለደረቅ ሁኔታ ተጋላጭ ከሆኑ አገሮች መካከል ናቸው። እንዲሁም በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ፣ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና በካሪቢያን የሚገኙ ሌሎች ሀገራት መሰል ሁኔታ ይገጥማቸዋል ተብሏል።
የዘንድሮው ኤልኖ በተለምዶ የአለምን አማካይ የሙቀት መጠን ከፍ ያደርገዋል እናም በ2016 ከተመዘገበው ከፍተኛ መጠን ጋር ተመሳሳይነት ሳይኖረው አይቀርም ተብሏል፣ ይህም የተለያዩ የካርበን ልቀት አደጋዎች እየተከሰቱ ባለበት ወቅት በመሆኑ እዚህም ላይ የራሱ ተፅእኖ ይኖረዋል ተብሎ ተሰግቷል። ለምሳሌ በኢንዶኔዥያ የደን እና መሬቶች ላይ ቃጠሎዎች በማስከተልም ውድመት ሊያደርስ ከመቻሉም በላይ የአለማችን ትልቁ በሆነው በአማዞን ደን ላይም ድርቅ አስከስቶ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎች ሊያወድም ስለሚችል በካርቦን ልቀትና የአለም ሙቀት ላይ ማባባስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የአለም አቀፉ የምግብና የእርሻ እንዲሁም የሚትርዮሎጂ ድርጅቶች ስጋታቸውን ገልፀዋል።