በ አፍሪካ ደረጃ የ ጂን ኢዲቴንግ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ግንዛቤን ለማሳደግና አቅምን ለማዳበር የሚረዱ የስልጠና ሞጁሎችን ለመገምገም የ ሶሰት ቀናት አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሂድ ይገኛል።
አውደ ጥናቱ የ ኢትዮጵያ ባዮና ኢምርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከ AUDA-NEPAD ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ከ አስር ከሚበለጡ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የ ባዮቲክኖሎጂ ባለሙያዎች እየተገመገመ ይገኛል።
የኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ በአወደ ጥና ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አፍሪካ ብዙ ያልተጠቀመችው ሀብት እንዳላት በመጠቆም ከነዚህ ውስጥም ብዙ የሚሰራ እንዲሁም የሚፈጥር ወጣት ያሉባት አህጉር በመሆና ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በመታገዝ የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል ብሎም መለውጥ ይቻላል ብለዋል። አክለውም የጂን ኢዲቴንግ ቴክኖሎጂ በግብርናው ዘርፍ ለውጥ እንደሚያመጣ በመግለጽ የተዘጋጀው መድረክ ለአፍሪካም ብሎም ለኢትዮጵያ ውቅቱ የጠበቀ እና ሚ/ቤቱ ከያዛቸው እቅዶች ጋር ተያያዝነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም AUDA-NEPAD እያደረግ ያለውን ድጋፍ በማመስገን ለወደፊትም አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እና ሚ/ር መ/ቤቱም በሚጠበቅበት ደረጃ ድጋፍ መስጠት እንደሚቀጥል በማሳወቅ በኢትዮጵያ ጥሩ የስራ ጊዜ እንዲያሳልፉ በመመኝት አውደ ጥናቱን ከፍተዋል።
ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ የ ኢትዮጵያ ባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይርክተር በበኩላቸው ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጂ በግብርና፣በጤና፣በኢንዱስትሪ እና በአካባቢ ላይ እንዲሁም የ ሰው ልጅን ህይወት ከመቀየር አንጻር ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ የዘመኑ ቴክኖሎጂ መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያም ከ 1980 ጀምሮ በስፋት ቢተገበረም ሕብረተሰቡ ላይ ለውጥ ከማምጣት አንጻር ብዙም አልተሰራም።
መንግስት የቴክኖሎጂውን ዘረፈ ብዙ ጥቅም በመረዳቱ ዘርፉ ራሱን ችሎ እንዲቋቋም እና በሀገር ደረጃ የሚሰሩ ምርምሮች እንዲሁም የልማት ስራዎች በተቀናጀ መልኩ የሕብረተሰቡን ችግር እንዲቀርፉ ዘረፉ በሀገር ደረጃ የሚያስተባብርው ተቋም እንዲኖር በመታመኑ የቀደሞው ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲሁም በአሁኑ የኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ተደርጓል።
ዶ/ር ካሳሁን በንግግራቸው ኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂን ለመጠቀም አመቼ ሁኔታዎች እንዳሉ በመጠቆም ሀገሪቷ ያላት የባዮሴፍቴ ህጎች፣ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች እና ምርምር ተቋማት ያሉ የሰው እና የ ላፕራቶሪ አንፍራስትራክቸር እንደ ምቹ ሁኔታ በመውሰድ ስራዎች መጀመር እንደሚቻል እና ሀገሪቷ ከቴክኖሎጂው መጠቀም ያለባትን ነገር መጠቅም እንዳለባት ጠቁመዋል።
ማህበረሰቡ በቴክኖሎጂ ዙሪያ የተሳሳተ አመለካከት እንዳይኖረው ከ AUDA-NEPAD ጋር በመተባበር ለሶሰት አመት የሚቆይ ሀገራዊ የሆነ የጂን ኢዲቲንግ ቴክኖሎጂ ኮምኒኬሽን ስትራቴጂ ያዘጋጀች ሲሆን ይህም መድረክ ስትራቴጂውን ለመተግብር አንድ እርምጃ ወደ ፊት ይውስዳናል። በ መጨረሻም ለአፍሪካ የ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና ግብርናና ለማዘመን የጂን ኢዲቴንግ ቴክኖሎጂ ጠቃሚ በመሆኑ AUDA-NEPAD በ አፍሪካ ደረጃ የሚሰራውን ስራ በማድነቅ ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል መለክታቸውን አስተላልፈዋል።
የተከበሩ ወ/ሮ ፍሎረንስ ናዛሪ፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት በAUDA-NEPAD ፣ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቪሽን ሴንተር ሀላፊ በበኩላቸው የአፍሪካን ኢኮኖሚ ለመቀየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ድርጅታቸ አባል ሀገርት በዘርፉ የሚሰሩትን ስራዎች የመደገፍ ብሎም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ከዚህም ጋር በታያያዘ በባዮ ቲክኖሎጂ በተለይም ሀገራት በጂን ኢዲቴንግ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን የተለያዩ ስራዎችን እይተሰራ እንደሆነና ሀገራት ለቴክኖሎጂው የ ኮምኒኬሽን ስትራቴጂ እንዲያዝጋጁ ድጋፍ የተደርገ ሲሆን ስትራቲጅውን ለመተግበር የተለያዩ የስልጣና ሞጅሎች ተዘጋጅተዋል።
ይህም መድረክ የተዘጋጁትን ሰነዶች የሚገመገሙበት ሲሆን ኢትዩጵያም መድረኩን በማዘጋጀት እንዲሁም ስትራቲጂውን በመተግብር ያሳየችውን ጥሩ አፈጻጽም በማደነቅ ሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንዲወስዱ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የ ኢትዮጵያ መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍ አመስነዋል።
(የኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)